foto1
foto1
foto1
foto1
foto1


ጥራት ያለዉ፤ በፈጠራ ላይ የተመሰረተና ቀልጣፋ የምህንድስና አገልግሎት ለመስጠት እንተጋለን!! We Strive to deliver quality, innovative and timely engineering service!!
Email:
Subject:
Message:

Visitors Counter

113805
Last Week
This Month
Last Month
All days
112219
1101
3757
113805

Latest News

Vacancy 2019-11-19 - More detail
Announcement 2019-11-19 -  a More detail
Projects 2019-11-19 -                  ... More detail

Login Form

http://www.gafatendowment.com

 

Gafat Endoment

 

ተልዕኮ

ከተለያዩ ለጋሽ አካላትና ከኢንቨስትመንት ሃብት በማሰባሰብና መልሶ ስትራቴጂክ በሆኑና የገበያ ጉድለት በሚታይባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በማሰማራት የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣትና በማህበራዊ የልማት መስኮች በመሳተፍ ለክልሉ ህዝብ የኑሮ ደረጃ መሻሻል እገዛ ማድረግ፡፡

ረዕይ

እ.ኤ.አ በ2030 በክልሉ ቀዳሚ የበጎ አድራጎትና የልማት አጋር ተቋም ሆኖ ማየት፡፡

ጋፋት ኢንዶውመንት በክልሉ ፍትህ ቢሮ መንግስታዊ ባልሆነ ዘላቂ የበጎ አድራጎት ድርጅትነት ጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም እውቅና አግኝቶ ተቋቋመ፡፡ ኢንዶውመንቱ ሲቋቋም በዋነኝነት ሁለት ተልዕኮወችን አንግቦ ነው፡፡የመጀመሪያው ከኢንቨስትመንት የሚያገኘዉን ሀብት ለበጎ አድራጐት ሥራዎች በማዋል የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ ማገዝና ለህዝብ ኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢንቨስትመንት መስኮች የሚገኘውን ትርፍ መልሶ ስትራቴጂክ በሆኑ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ በክልሉ ውስጥ የሥራ እድልን መፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማምጣት ነው፡፡

እነዚህን ተልዕኮወች ለማሳካት በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ የሚገኙ አራት ኩባንያወችን ማለትም፡-

             1ኛ.ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

               2ኛ. ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

               3ኛ. መቅደላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

               4ኛ. ላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ጋፋት ኢንዶውመንት ከላይ በጠቀስናቸው ኩባንያዎች አማካኝነት በሚያከናውናቸው የልማት ስራወች ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ከኢንቨስትመንት በሚያገኘው ገቢ የማህበራዊ ልማት ስራወችን በማከናወን የክልሉን ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ በዚህም የገቢ ማስገኛ ኩባንያዎቹ ከሚፈጥሩት ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ባሻገር በማህበራዊ ልማት መስክ በጀት በመመደብ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ ይገኛል፡፡ለዚህም በያዝነው የፈረንጆቹ 2018 በጀት አመት ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ለ 200 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር አቅዶ በመስራት ላይ መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡  

ኢንዶውመንት በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በአበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ በመሳተፍ ክልሉ ለሆርቲካልቸር ልማት ምቹ መሆኑን በማሳየት ሌሎች ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ በማስቻል ክልሉ በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን አምባሳደር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡

በቀጣይም የኢንቨስትመንት አድማሱን በማስፋፋት በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ቅድመ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ኢንዶውመንቱ ገና በለጋ እድሜ ላይ ቢሆንም በቆየባቸው ጥቂት አመታት ተልዕኮወችን ከማሳካት አኳያም ሆነ  የክልሉን ልማት በመደገፉ ሂደት ያከናወናቸዉ ተግባራትና በሂደቱም ያስመዘገባቸው ውጤቶች ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡ይህን ተልዕኮውን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ውጤታማነቱንም ይበልጥ ለማጎልበት የኢንዶውመንት ጽ/ቤቱንም ሆነ የገቢ ማስገኛ ተቋማቱን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

News

በምህንድስና፣በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ደረጃ በጥራት እና በብቃት ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ እ.ኤ.አ.በ2030 ተፈጥሮ ማየት፡፡

በብቁ ባለሙያዎች ጥራት ያለው፣ በፈጠራ ላይ የተመሰረተና ቀልጣፋ የምህንድስና አገልግሎት በታማኝነት የመስጠት መርህን አንግቦ በ 2008 ዓ.ም የተመሰረተው ላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ሌላኛው የጋፋት ኢንዶውመንት ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው በውሃ፣በመንገድና ህንጻ ስራዎች ዘርፍ የጥናት፣ዲዛይንና ሱፐርቪዥን አገልግሎት፤በንግድና ኢንቨስትመንት የጥናትና የማማከር እንዲሁም የአከባቢ ተጽእኖ ግምገማና ጥናት አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡


Language

Minicalendar

December 2022
SMTWTFS
123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728293031

Facebook Like