ንገነባ ዛሬን ሳይሆን ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ በማድረግ ነው!!
መቅደላ ኮንስትራክሽን በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት ተመዝግቦ የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ኩባንያው ጋፋት ኢንዶውመንት የበጎ አድራጎት ስራውን ለማከናወንና እና በአማራ ክልል የገበያ ክፍተት የሚስተዋልባቸውን የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሙላት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ሃብት ለማመንጨት ካቋቋማቸው አራት ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
ኩባንያው በክልሉ ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን በዘርፉ የክልሉን መንግስት ጥረት ለመደገፍ በ2004 ዓ.ም የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡
መቅደላ ኮንስትራክሽን በአማራ ክልል ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ በሚካሄዱ የመንገድ፤ የድልድይ እና የህንፃ ግንባታ ስራዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አዋጭነት ያለው እና የአካባቢ ደህንነትን ባገናዘበ ሁኔታ በመገንባት ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ የማድረግ ተልዕኮ እና እ.ኤ.አ. በ2030 በመንገድ፣ በድልድይ እና በህንፃ ግንባታ ዘርፍ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ አርኪና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ መሆንን ረዕይው አድርጎ ይህን ለማሳካት እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
ይህነ ለማሳካትም የሚከተሉትን እሴቶች የእለት ተእለት የስራ መመሪያው አድርጎ የሚንቀሳቀስ ኩባንያ ሲሆን እነዚህም፡-
የሚሉት ናቸው፡፡
ኩባንያው ታማኝነት፣ጥራትና ቅልጥፍናን መርሁ በማድረግ በድልድይ፣በመንገድና በህንጻ ግንባታ ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን የማከራየት አገልግሎትም ይሰጣል፡፡